አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ይፋ ባደረገው የሙስና ቅኝት የ2020 ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የነበራትን ደረጃና ውጤት ማሻሻሏን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ከነበረችበት 96ኛ ደረጃ ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል 94ኛ ስትሆን ያስመዘገበችውም ውጤት ከ37 ወደ 38 አድጓል፡፡
ሀገራችን ከሁለት ዓመታት በፊት የነበራት ደረጃ 114ኛ ሲሆን ውጤቷም 34 ነበር፡፡
ሪፖርቱ እንዳመለከተው ከ180 ሀገራት ውስጥ ዴንማርክና ኒውዚላንድ 88 ነጥብ በማምጣት የመሪነት ደረጃ ላይ ሲቀመጡ÷ ፊንላንድ፣ ሲንጋፖር፣ ስዊዲንና ሲዊዘርላንድ ደግሞ 85 በማምጣት ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በተቃራኒው ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ 12 ነጥብ በማምጣት የመጨረሻውን ደረጃ የያዙ ሲሆን ሶሪያ 14፣ የመን 15 እንዲሁም ቬኒዞላ 15 ነጥብ በመያዝ ይከተላሉ፡፡
እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዚህኛው ዓመትም ከሁለት ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት ከ50 ነጥብ በታች ያስመዘገቡ ናቸው፡፡
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በየዓመቱ የሙስና ቅኝት ጥናት በማካሄድ የሀገራትን የሙስና ሁኔታ የሚየሳይ ደረጃና ውጤት ይፋ የሚያደርግ መቀመጫውን ጀርመን ያደረገ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም መሆኑን ከሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!