አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)እንግሊዝ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ድጋፍ ልታደርግ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀንን አቅም ለመደገፍ እና ለመገንባት እንግሊዝ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሚታወስ ሲሆን፤ እንግሊዝ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሶስት አገራት የ3 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ድጋፍ እንደምታደረግም ነው የገለጹት፡፡
ድጋፉ በቢቢሲ ሚዲያ አክሽን የሚመራ ሲሆን፤ የመገናኛ ብዙኀንን መደገፍ ሃሰተኛ መረጃዎችን ለመቆጣጠር እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ በሚዲያ ተቋማቱን እና በሚዲያ ተከታዩ ህብረተሰብ ላይ ያደረሰውን ተጽእኖ የሚያመላክት ሲሆን፤ ተቋማቱ በፋይናንስ ራሳቸውን መደገፍ እንዲችሉ ማስገንዘብ ነው፡፡
እንግሊዝ ለመገናኛ ብዙኀን የምትሰጠው የአቅም ግንባታ በታዳጊ አገሮች የምታደርገው ድጋፍ አንድ አካል መሆኑንም ከእንግሊዝ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!