አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴና የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት /ተመድ/ የ26ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ ፕሬዚዳንት አሎክ ሻርማ ጋር በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአየር ንበረት ለውጥን ከመከላከል አኳያ የአረንጓዴ ልማት ተግባሮችን መልሶ ማቋቋም ስለሚቻልበት ሁኔታ መክረዋል።
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚካሄዱ የልማት ስራዎች ተፈጥሮ ላይ ለሚከሰቱ ችግሮች ተፈጥሯዊ ምላሽ ለመስጠት ቁልፍ ሚና እንደሚኖራቸውም በውይይቱ መነሳቱን ኢዜአ ዘግቧል።
26ኛው የተመድ የአየር ንበረት ለውጥ ጉባኤ በፈረንጆቹ 2021 መገባደጃ በስኮትላንድ ግላስኮው እንደሚካሄድ ተነግሯል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!