የሀገር ውስጥ ዜና

አንዳችን ለሌላችን እናስፈልጋልን -አቶ አገኘሁ ተሻገር

By Abrham Fekede

January 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እኛ ኢትዮጵያኖች በጋራ ስንሆን ለእኛ ውበትና ጉልበት ነዉ ሲሉ ተናገሩ።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እኛ ኢትዮጵያኖች በጋራ ስንሆን ለእኛ ውበትና ጉልበት ነዉ ፤ አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ብለዋል፡፡

እኛን ለማይፈልጉ ግን ቆም ብለዉ ሁለቴ ፣ ሦስቴ እንዲያስቡ እድል ይሰጣል ያሉ ሲሆን የመንግሥታት ሕጋዊ ግንኙነት አስፈላጊነት አጠያያቂ አይሆንም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ይህ ደግሞ የዜጎችን የመኖር መብትንም ለማስጠበቅ ዕድል ይሰጣል ነው ያሉት።

ስለዚህ በክልሎች መካከል በመንግሥታት የግንኙነት ሕግ መሠረት ግንኙነታችን ማጠናከር አለብን ሲሉም አሳስበዋል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተዘጋጀው የሰሜንና ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የምክክር መድረክ  “መልካም ጉርብትና ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በባህር ዳር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!