የሀገር ውስጥ ዜና

ተጨማሪ 549 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 266 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

By Meseret Demissu

January 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 3 የላቦራቶሪ ምርመራ  549 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 266 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 2 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት 2 ሺህ 85 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 647  ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 230 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 942 ሺህ 333 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!