የሀገር ውስጥ ዜና

የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት ውይይት በሀረር ከተማ ተጀምሯል

By Abrham Fekede

January 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት ወይም ፓትሮል የውይይት መድረክ በሀረሪ ህዝቦች ክልል ሀረር ከተማ መካሄድ ተጀምሯል፡፡

መድረኩ የክልሎችንና ከተማ አስተዳደሮችን የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የሰላምና ደህንነት አመራሮችን ያሳተፈ የገለልተኛ አማካሪ ቡድን መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ያዘጋጀው ይኸው የውይይት መድረክ ከዛሬ ጥር 22 እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት/ፓትሮል ሥራ በሀገራችን በሁሉም መዋቅሮች ተግባራዊ እንዲሆን ለመምከር የተዘጋጀ ነው፡፡

የገለልተኛ አማካሪ ቡድንና የማህበረሰብ ደህንነት ቅኝት/ፓትሮል እና የፖሊስ ዶክትሪን የሰነዶች ዝግጅት ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ደመላሽ ካሣዬ ስራው በየክልሎቹ ለሚፈጠሩ የሰላም ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉበዔ ወ/ሮ አዲስዓለም በዛብህ መድረኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!