የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ በኦሮሚያ ክልል በመስኖ የለማ ስንዴ ጎበኙ

By Abrham Fekede

January 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የበኦሮሚያ ክልል በመስኖ የለማ የቆላ ስንዴን ጎበኙ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል በ130 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቆላ ስንዴን በመስኖ የማምረት ሥራ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ይህም በ300 ሺህ ሄክታር ላይ ሊከወን የታቀደው ሥራ አንድ አካል መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

በተጨማሪም ከውጪ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ያለውን ፍላጎት እና ዐቅም በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን