አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን ሰዴ ሙጃ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ24 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
መነሻውን ከባሕር ዳር ያደረገው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሰዴ ሙጃ ወረዳ ሲደርስ 200 ሜትር ከሚረዝም ገደል በመግባቱ የ24 ሰዎች ህይወት ማለፉን የደቡብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ጋሻው አለኸኝ ተናግረዋል ፡፡
በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በደብረታቦርና በፈለገሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ኮማንደር ጋሻው በስልክ ገልፀዋል፡፡
የአደጋው መንስዔ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ኮማንደሩ ማናገራቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!