አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ አካል ዳርቻ ክልልን ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ የባለሙያዎች ውይይት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት፣ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፈቲያ የሱፍን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል ባለድርሻ አካላትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተሳታፊዎች ናቸው።
በረቂቅ አዋጅ ላይ የሚደረገው የባለ ድርሻ አካላት እና ምሁራን ውይይት ተጨማሪ ግብዓት ለማግኘት እና በሚሻሻሉ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑን የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው ተናግረዋል።
ረቂቅ አዋጁ በስድስት ክፍሎች እና በ28 አንቀጾች ተከፍሎ የቀረበ ሲሆን 23 ሙያዊ ቃላትም ትርጓሜ እንደተዘጋጀላቸው ተገልጿል።
በናትናኤል ጥጋቡ