የሀገር ውስጥ ዜና

በተያዘው አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ 3 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው

By Feven Bishaw

February 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በተያዘው በጀት አመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ 3 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለፋት ስድስት ወራት የስራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የየክልሎቹ የኢተርፕራይዝና የስራ ዕድል ቢሮዎች ፣ የፌዴራል የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እንዲሁም የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አመራሮችና የመገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የፌዴራል የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን፥ የስራ እድል ፈጠራውን ለማሳካት እና ለ 3 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድሉን ለመፍጠር በልዩ ትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።

የተያዘውን እቅድ ስኬታማ ለማድርግ እና የስራ አጥነት ችግርን ለመፍታትም ወሳኝ የሆኑትን የመንግስት እና የግል ኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት እንዲሁም አዳዲስ የስራ እድል ዘርፎች መፍጠር እንደሚጠይቅም ተጠቁሟል።

በዚህም አዳዲስ የስራ ክህሎቶችን ማዳበር እና ማጎልበት፣ እንዲሁም የስራ ገበያውን ፍላጎት እና አቅርቦት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ላይም እንደሚሰራ ነው አቶ ንጉሱ የጠቆሙት።

በ2013 አመትም የተያዘው የ 3 ሚሊየን ሀገራዊ የስራ እድል ፈጠራ እቅድ እና እስካሁን የተሰራው ሀገራዊ የስራ እድል ፈ-ጠ አፈፃፀም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው ምክር ቤት ተገምገሞ ከፀደቀ በኋላ ይፋ ይደረጋልም ተብሏል።

በመድረኩ የፌደራል፣ የአስሩም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ምክክር እንደሚካሄድባቸው ይጠበቃል።

መድረኩ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል።

በፀጋ ታሪኩ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!