አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የምርጫ ቦርድን ይጠይቁ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎ መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡
የምርጫ ቦርድ በማህበራዊ ሚዲያው እንዳታወቀው በምርጫ ጉዳይ ብቻ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጥያቄዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡
ቦርዱ ባዘጋጀው በዚሁ የማህበራዊ ሚድያ ተሳትፎ መድረክ ጥያቄዎችን በምርጫ ቦርድ ገፅ መልእክት መስጫ በኩል እንዲሁም በአስተተያየት መስጫው ላይ መላክ ይቻላል ተብሏል፡፡
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሐሙስ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም በፌስቡክ ገፁ ላይ በቀጥታ በመግባት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!