አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትሰራ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገለጹ።
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ለኢዜአ እንደገለጹት ጃፓንና ኢትዮጵያ በርካታ ዓመታት የዘለቀ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አገራት ናቸው።
ጃፓን የኢትዮጵያን የልማት ሥራዎች በፋይናንስ ጭምር በመደገፍ አጋርነቷን ማሳየቷን ነው የተናገሩት።
ሀገራቸው በተለይ በሥራ እድል ፈጠራና ወጣቶችንና ሴቶችን በተለያዩ የሙያ ሥልጠናዎች የማብቃት ሥራ ላይ ትኩረት አድርጋ ድጋፍ እንደምታደርግም አንስተዋል።
በግብርና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪና የተለያዩ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን በመደገፍ ረገድም ጃፓን ትልቅ ሚና እንዳላት ጠቁመዋል።
ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የልማት ትብብር ይበልጥ አጠናክራ መቀጠል እንደምትሻም አምባሳደሯ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረጓ ደግሞ ለሁለቱ ሀገራት ትስስር መሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለውም ነው የተናገሩት።
“ይህንንም ጃፓን በአዎንታዊ መልኩ ትመለከተዋለች” ብለዋል።
ኢትዮጵያና ጃፓን የሁለትዮሽ የወዳጅነትና የንግድ ግንኙነት ለመጀመር ከተፈራረሙ 90 ዓመት ያስቆጠሩ ሲሆን፤ ግንኙነቱ በመካከል በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።
ተቋርጦ የነበረው የአገራቱ ሁለትዮሽ ግንኙነት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ዳግም ከተጀመረ 65ኛ ዓመቱን ይዟል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!