የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ በነገው መደበኛ ጉባኤው የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል

By Tibebu Kebede

January 08, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነገው ዕለት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

በስብሰባውም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ነው የተነገረው፡፡