አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሶስት ዞኖችን የሚያስተሳስረው የዱር ቤቴ -ሻውራ ገንዳ ውሀ የአስፓልት መንገድ ግንባታ በዚህ አመት እንደሚጀመር የኢትጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ መንገዱን ወደ አስፓልት ደረጃ ለማሳደግ በሶስት ኮንትራት ጨረታ መውጣቱንና የአንደኛው ኮንትራት አሸናፊ ተለይቶ ውል መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
መንገዱ ከጣና ሀይቅ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የሚገኙትን የምዕራብ ጎጃም፣ የማዕከላዊ ጎንደርና የምዕራብ ጎንደር ዞኖችን የሚያስተሳስር ብሎም ወደ ጎረቤት ሱዳን የሚያደርስ መንገድ ነው፡፡
የመንገዱ በአስፓልት ደረጃ መገንባት የአካባቢው አምራች ገበሬዎች ምርታቸውን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስና የማህበረ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለማሳለጥ እንደሚረዳ ታምኖበታል፡፡
በነብዩ ዮሐንስ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!