አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 31/3/ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
እንዲሁም አንቀፅ 32/2 ደግሞ የፓርቲዎች እጩዎች በሕጉ መሠረት መሰብሰብ የነበረበት የድጋፍ ፊርማ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ብቻ ተፈፃሚ እንዳይሆን እንዲታገድ መደረጉ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የሚያግዝ ሆኖ በመገኙቱ ይህ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀበት ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የፀና እንደሚሆን የሕግ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን ውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል።
አንቀፅ 32 (2) የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡
ይሁን እንጅ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በዚህ ዓመት በሚደረገው ምርጫ የወረቀት ልውውጥ እና ንክኪን በተቻለ መጠን መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ ባለው የተጣበበ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የተነሳ ከፓርቲዎች ፊርማ ለማሰባሰብ በቂ ጊዜ ስለማይኖራቸው በቦርዱ በኩል ያለው ሁኔታም ተመሳሳይ ስለሚሆን ለማጣራት ስለሚቸግረው እና በፖለቲካ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ከፍተኛ ቅሬታ የሚቀርብበት በመሆኑ ።
ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብቻ ተግባራዊ እንዳይሆን ለማገድ መወሰኑ ተገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!