አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ከመከላከያ ሰራዊት ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
የመከላከያ ሰራዊት በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ወቅት ያሳካቸውን ዋና ዋና ተግባራቶች በቆይታቸው ዘርዝረዋል።
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የመከላከያ ሰራዊት ህግን የማስከበር እርምጃ ኢትዮጵያን ከእርስ በእርስ ግጭት እና ከመበታተን ታድጓል ብለዋል፡፡
ጦርነት በራሱ ፣ ህግ የማስከበር ስራ ነውና ፣ ጁንታው የጀመረውን ጦርነት በማክሸፍ የሀገር ሉአላዊነትን በማስጠበቅ የህግ የበላይነትን
አረጋግጧል ነው ያሉት፡፡
ጦርነቱን በሳምንታት በመጨረስ የተራዘመ ውጊያ በማስቀረት በአነስተኛ ኪሳራና በአጭር ጊዜ ለድል በቅቷልም ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በውጊያ ውስጥ በመሆን ከ700 ኪሎ ሜትር በላይ በመጓዝ ፤ እያንዳንዱን ተራራ ከጠላት በማፅዳት ፤ ምሽግ በመስበር እርምጃ እንደወሰደ ተናግረዋል፡፡
ሰራዊቱ በግጭት አካባቢ ለሚገኘው ህዝብን ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ጁንታው ከፈፀማቸው ጥፋቶች ውጭ ንብረት እንዳይወድምና ሰላማዊ ዜጋ ነዋሪ እንዳይጎዳ በከፍተኛ ሁኔታ ተከላክሏል ብለዋል፡፡
ጄኔራል ብርሃኑ የጁንታው አመራሮችን ከየተደበቁበት ዋሻ በመግባት በቁጥጥር ስር አውሏል ፤ አሻፈረኝ ያሉትንም ደምስሷል በማለት አብራርተዋል፡፡
ጁንታውን ከነወታደራዊ አቅሙ ደምስሶታል፤ ፍትሀዊ ጦርነት በማድረግ የጁንታውን ኢ-ፍትሀዊ ሙከራን
አክሽፏል ብለዋል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ፡፡
ሀገርን ለማፍረስ በይፋ ሲንቀሳቀስ የነበረ ፤ የሀገር ጠንቅና የህዝቡ የስቆቃ ምንጭ የሆነውን የጁንታው ሀይል እንዳይመለስ አድርጎ ቀብሮታል ያሉት ጄኔራል ብርሃ ታሪክ ሆኖ እንዲቀርም አድርጎታል ብለዋል፡፡
በመስዋዕትነቱ ለሀገር መረጋጋት በማምጣቱ የሰራዊቱ ስራ ለዘመናት ሲዘከር የሚኖር ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!