የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሊያ መንግስት የደቡብ ምዕራብ ክልል ልዑክ በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች ሁኔታ እና በሰላምና ፀጥታ ላይ ለመምከር ጅግጅጋ ገባ

By Tibebu Kebede

February 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ መንግስት የደቡብ ምዕራብ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊ ልዑክ በሶማሊያ በሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ሃይሎች ሁኔታ እና ከሶማሌ ክልል መንግሥት ጋር በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ለመወያየት ጅግጅጋ ገባ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ሶማሊያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ሃላፊና የከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ የሚመራ ልዑክ፣ በጅግጅጋ ጋራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በሶማሌ ክልል የጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መሀመድ አህመድና በአፍዴር ዞን አስተዳደሪ አቶ መሀመድ አብዲ ሀሞና በሌሎች የክልሉ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።

በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል የከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ በሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ሃይሎች በሁለቱ ሀገራት ድንበር የጸጥታ ችግር እንዳይፈጥሩ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን በትብብር ለመስራትና ከሶማሌ ክልል መንግሥት ጋር በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ለመወያየት መሆኑን ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!