አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የድጋፍ ሰልፎች በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተካሄዱ፡፡
የድጋፍ ሰልፎቹ፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በጉጂ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እንዲሁም በቢሾፍቱና ሞጆ ከተሞች ነው የተካሄዱት፡፡
ከዚህ ባለፈም በአምቦ፣ ለገጣፎ፣ መቱ፣ ሰንዳፋ በኬ እና ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማም የድጋፍ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ ላይ በሃገሪቱ እየተመዘገበ ያለውን የለውጥ ተግባር የሚያደንቁ ሃሳቦች ተንጸባርቀዋል፡፡
ሰልፈኞች ይዘዋቸው በወጡ የድጋፍ ድምጾች የኢትዮጵያን ህልውና ለማስጠበቅ ከመንግስትና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደር ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
ሰልፈኞቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተመዘገበው ውጤት ዕውቅና የሰጡ ሲሆን፥ ከምርጫ ውጪ በጉልበትና በሀይል ስልጣን ለማግኘትና ለውጡን ለመቀልበስ የሚሰሩ ቡድኖችን አውግዘዋል።
ባሰሟቸው መፈክሮችም ‘የኦሮሞ ህዝብ የአጥፊዎች ዋሻ አይደለም’፣ ብለዋል።
“ጀግኖችን ማወደስና ማክበር የኦሮሙማ እሴት ነው፤ በጁንታው መቃብር ላይ ብልፅግና፥ ሰላምና የህዝቦች አንድነት ይለመልማል፤ የተጀመሩ የህግ የበላይነት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ፤ የኦነግ ሸኔን አጥፊ ተግባር እናወግዛለን” የሚሉ መፎክሮች ተስተጋብተዋል።
ሃገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍ የሚያሴሩ ሃይሎችን በቁርጠኝነት እንደሚታገሉም አረጋግጠዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!