የሀገር ውስጥ ዜና

በመቐለ ከተማ ትምህርት የካቲት 1 ቀን ይጀመራል

By Tibebu Kebede

February 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግን  የማስከበር እርምጃ እና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የከተማዋ ከንቲባ አስታወቁ።

በከተማዋ ትምህርት መጀመሪያ በኮሮና ምክንያት በኋላም በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱን የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አታክልቲ ኃይለስላሴ ለኢፕድ ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት የከተማዋ ሰላምና ጸጥታ የተረጋጋ በመሆኑና የኮሮና ቫይረስ ለመከላከያ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ በሁሉም ደረጃ ባሉ የትምህርት ክፍሎች ከየካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም አንስቶ ትምህርት መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

ወላጆች ልጆቻቸውን ከተጠቀሰው እለት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩም አቶ አታክልቲ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም ከንቲባው አስታውቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!