አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራኑ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሮሃኒ ሃገራቸው በቀጣዮቹ ሳምንታት የኮቪድ19 ክትባት መስጠት እንደምትጀምር አስታወቁ፡፡
ክትባቱ ከፐርሺያኖቹ አዲስ አመት መባቻ ቀደም ብሎ እንደሚጀምርም ገልጸዋል፡፡
በክትባት ዘመቻውም የህክምና ባለሙያዎችና ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡
የክትባት ዘመቻው ከመጀመሩ አስቀድሞ በሚሊየን የሚቆጠር ክትባት ከውጭ ሃገራት የማስገባት ስራ ይሰራልም ነው ያሉት፤ በቀጣይ በሃገር ውስጥ የተዘጋጁ ክትባቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ በመጥቀስ፡፡
ኢራን ለኮቪድ19 መከላከያ 16 ነጥብ 8 ሚሊየን ክትባቶችን ከኮቫክስ ገዝታለች፡፡
ከዚህ ባለፈም ከሩሲያ ክትባት የገዛች ሲሆን ተጨማሪ ክትባቶችን ከቻይና እና ህንድ ለመግዛት ስለማሰቧም ነው የተሰማው፡፡
ከዚህ ባለፈ ግን ቴህራን ሃገር በቀል የህክምና ውጤቶችን በመጠቀም ክትባት ያዘጋጀች ሲሆን ባለፈው ታህሳስ ወር ላይም አንደኛውን ክትባት መሞከሯ ተገልጿል፡፡
በኢራን 1 ሚለየን 431 ሺህ 416 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው 58 ሺህ 110 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ምንጭ፦ ፕረስ ቲቪ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!