የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የደቡብ ክልል መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ምክክር እያካሄዱ ነው

By Meseret Awoke

February 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች እና የደቡብ ክልል መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ በደቡብ ክልል የሚሰሩ መጠጥ ውሃ ፣ የመስኖና ኢነርጂ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዙሪያ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ።

በምክክር መድረኩ የኢፌዴሪ የውሃና መስኖ ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ውሃ ለዜጎች ህይወት መቃናትና ኑሮ መሻሻል እጅግ መሰረታዊ ነገር በመሆኑ ካለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ በዋሽ አንድና በዋሽ ሁለት በተጀመሩ ፕሮጀክቶች በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ሲሆን፤ በገጠርና በከተማ በርካታ ዜጎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

ሆኖም ግን ከክልሉ ፍላጎት አኳያ ሽፋኑ ዝቅተኛ በመሆኑ የንጹህ መጠጥ ውሃ የሚያገኙ ዜጎች ከ40 በመቶ ያልበለጠ እንደሆነና የተጠናከረ ስራን እንደሚጠይቅ አንስተዋል።

በቀጣይም የክልሉ የፕሮጀክት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!