የሀገር ውስጥ ዜና

የዶክተር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን ምስረታ ይፋ ተደረገ

By Tibebu Kebede

February 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዶክተር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን ምስረታ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል።

ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በጤና ፣ በአረንጓዴ ልማት ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ እውነትንና ሀቀኝነትን ይዞ የሃገርን ልማት የሚያግዝ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

የዶክተር አምባቸው መኮንን ራእይ የሚያስቀጥል ፋውንዴሽን ለማቋቋም የተደረገውን ጥረትም ምክትል ከንቲባዋ አድንቀዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ብሎም በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚታዩ ማህበረሰባዊ ችግሮችን በማቃለል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ደግሞ ሌላኛው የፋውንዴሽኑ ዓላማ ይሆናል ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ሚኒስትሮች፣ የዶክተር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን የቦርድ አመራር አባላት እና የዶክተር አምባቸው መኮንን የቅርብ ወዳጆች እና ቤተሰቦች መገኘታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!