አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የማይናማር ጦር ያካሄደው መፈንቅለ መንግስት ስኬታማ እንዳይሆን ለዓለም ሀገራት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዋና ጸሐፊው በጥሪያቸው የምርጫ ውጤትን መቀልበስ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
አክለውም የመፈንቅለ መንግስቱ አመራሮች በዚህ መልኩ ሀገራቸውን ሊመሩ እንደማይችሉ ሊረዱ ይገባልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ ህገመንግስታዊ ስርዓት ዳግም እንዲመለስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ እየመከረ እንደሚገኝም የተገለጸ ሲሆን ምክር ቤቱም ተመሳሳይ አቋም እንደሚያንጸባርቅ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቷ ተመራጭ መሪ አሳን ሱ ኪ አሁንም በመፈንቅለ መንግስቱ አመራሮች የቁም እስረኛ ናቸው ተብሏል፡፡
የመፈንቅለ መንግስቱ ጁንታ በሚንግ ኡን የሚመራ ሲሆን 11 አባላትን ይዟል፡፡
ይህ 11 አባላትን የያዘው ጁንታ በሀገሪቱ ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡
በተጨማሪም ፌስቡክን ጨምሮ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶችን አግዷል፡፡
በሀገሪቱ መፈንቅለ መንግስቱን የሚቃወሙ አክቲቪስቶች በማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ እንደነበር ተሰምቷል፡፡
አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ የዓለም ሀገራት መፈንቅለ መንግስቱን በማውገዝ መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!