የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ ለሁለት ተከታታተይ  ቀናት በአርብቶ አደር እና መንግስታት  ግንኙነት ፖሊሲ ላይ ሲሰጥ የነበረው  ስልጠና ተጠናቀቀ

By Meseret Demissu

February 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታተይ  ቀናት በአርብቶ አደር ፖሊሲ  እና መንግስታት  ግንኙነት ፖሊሲ ላይ ሲሰጥ የነበረው  ስልጠና ተጠናቋል፡፡

ሰላም እና ልማት የማይነጣጠሉ ጉዳዮች በመሆናቸው በአርበቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ያሉትን የማህበረሰብ ክፍሎች ልማት በማመጣጠንና ኑሯቸውን በማሻሻል ግጭቶችን ለመቀነሰ የአርብቶ አደር ፖሊሲ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳላው በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ተገልጿል፡፡

በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ልዩ ድጋፍ ዳይሬክተር ጀነራል ፕሮፌሰር ደገፋ ቶሎሳ የስልጠናው ተሳታፊዎች በስራቸው ላሉ ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጡ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች የአርብቶ አደር ፖሊሲ እና መንግስታት ግንኙነት ፖሊሲ የታቀዳላቸውን ዓላማ ማሳካት የሚችሉ ፖሊሲዎች መሆናቸውን ገልፀው÷ በቀጣይ ለተግባራዊነታቸው የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ እንደሚሰሩ መግለጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!