አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከፖርቹጋል መከላከያ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜስ ክራቪኖ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በጂኦ ፖለቲካ ፣ በባህር ደህንነት ፣ ስደትን በተመለከቱ ጉዳዮች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በበይነመረብ መወያየታቸውን ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የፖርቹጋል ፕሬዚዳንት ኢጋድ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክረዋልም ብለዋል ዋና ጸሃፊው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!