የሀገር ውስጥ ዜና

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ሐረሪ ክልል ገባ

By Meseret Awoke

February 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣2013(ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሐረር ከተማ በተለምዶ ሀማሬሳ ከሚባለው አካባቢ ሲደርሰ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የአዲስ አበባ ከተማ ቆይታውን አጠናቆ ወደ ሐረር የተጓዘው የታላቁ ሕዳሴ ዋንጫ በሐረሪ ክልል የሚከናወነውን የግድቡ ግንባታ የገቢ አሰባሰብ ለማሳደግ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ከተማ በነበረው ቆይታው ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደተሰበሰበ ይታወቃል።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተማሪዎችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለዋንጫው አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!