የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመዝጋቢ ቁጥር ከባለፉት አስር ዓመታት አንጻር በዓመት የተመዘገበው ቁጥር በ500 ፐርሰንት እንደሚበልጥ ተገለጸ

By Tibebu Kebede

February 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመዝጋቢ ቁጥር ከባለፉት አስር ዓመታት አንጻር በዓመት የተመዘገበው ቁጥር በ500 ፐርሰንት እንደሚበልጥ ተገለጸ፡፡

አዲሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2013 ከወጣ እና ምዝገባ ከተጀመረ ጀምሮ ከ1 ሺህ 300 በላይ አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገባቸውን ተገልጿል፡፡

እድገቱ ከባለፉት 10 ዓመታት አንጻር በዓመት የተመዝጋቢው ቁጥር 500% የሚበልጥ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ዜጎች በህገመንግስቱ እና በአዋጁ የተቀመጠውን የመደራጀት መብት በአግባቡ እየተጠቀሙ መሆኑ እና ዘርፉ መነቃቃቱን ማሳያ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት በ6 ወራት አዲስ ለመመዝገብ ከተያዘው 354 እቅድ 355 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መመዝገባቸውን በመግለጽ የአዲስ የምዝገባ ፍቃድ የሚያወጡ ደንበኞች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እጨመረ መምጣቱን እና ይህም በቀን በአማካይ 8 ድርጅቶች እንደሚመዘገቡ የምዝገባ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ወርቁ ጠቅሰዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!