የሀገር ውስጥ ዜና

68 ዜጎች ከሊባኖስ ቤይሩት ተመለሱ

By Tibebu Kebede

February 05, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስልሳ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ከሊባኖስ ቤይሩት መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በፍሪደም ፈንድ እና አጋር ኢትዮጵያ በተባሉ አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች አማካኝነት ነው ወደ አገራቸው የተመለሱት። ወደ አገራቸው የተመለሱ ዜጎችን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!