የሀገር ውስጥ ዜና

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለመተከል ተፈናቃዮች ከሁለት ሺህ ኩንታል በላይ የስንዴ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Demissu

February 07, 2021

አዲስ አበባ ፣ ጥር 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመተከል ተፈናቅለው ቻግኒ ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ 48 ሺህ ተፈናቃዮች የሁለት ሺህ 800 ኩንታል የስንዴ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ያደረጉት የንግድና ኢንዱስትሪ  ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማት እንደሆኑ ተገልጿል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተፈናቃዮችን በመጎብኘት ድጋፉን አስረክበዋል።

በድጋፍ ርክክብ ወቅት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንዳሉት÷ሁሉም ዜጋ ርብርቡን በማጠናከር ለተፈናቃዮቹ የበለጠ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል።

ድጋፉ የተደረገው የንግድ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሆነ ገልፀው ሌሎች ተቋማትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽነር ዘላለም ልጅአለም ቤንሻንጉል ጉምዝን ጨምሮ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈናቀሉ 277 ሺህ ዜጎች በአማራ ክልል እንዳሉ ገልፀዋል።

የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት እና ከሌሎች አካላት የሰበሰበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮቹ ለማዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ኮሚሽነሩ  ተናግረዋል።

በመጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ሁሉም ዜጋ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!