አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በዘንድሮው በጀት ዓመት ከ526 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ አዳዲስ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን አስጀምሯል፡፡
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በተያዘው በጀት ዓመት በ526 ሚሊየን 343 ሺህ ብር ወጪ 14 ነጥብ 26 ኪሎ ሜትር የጌጠኛ መንገድ፣ 15 ኪሎሜትር አዲስ መንገድ ፣ ሁለት አዲስ ድልድዮች በበላይ ዘለቀ እና በፋሲሎ ክፍለ ከተማ ግንባታቸው መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ የሶስት የአረንጓዴ ቦታዎች በድሮው ዴፖ፣ ዳግማዊ ምኒሊክ ፣ አፄ ቴዎድሮስ እና በላይ ዘለቀ ክፍለ ከተሞች የተጀመሩ ሲሆን፥ 5ኪሎ ሜትር የውሃ የመስመር ዝርጋታ በመሸንቲ ከተማ ግንባታ መጀመሩን አስረድተዋል፡፡
ግንባታቸውም በ70 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ዶክተር ድረስ ሳህሉ ገልፀዋል፡፡
የመሠረተ ልማት ግንባታዎቹ በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ህብረተሰቡ አስፈላጊ የጊዜ እና የጥራት ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡
በተጨማሪ ከ900 ሚሊየን ብር በላይ በስድስቱም ክፍለ ከተሞች ግንባታቸው በመጠናቀቅ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ስራዎች መኖራቸው ተገልጿል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!