አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር የብድር ስምምነት ተፈራረመ ።
የብድር ስምምነቱ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚሰሩ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት እና ለተሽከርካሪ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።
የብድር ስምምነቱ እንዲከናወን የአየር መንገዱ ቀዳማዊ የሰራተኞች ማህበር ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል።
ብድሩ በአነስተኛ ወለድ ሰራተኛው እንዲጠቀም የሚያደርግ መሆኑን የአየር መንገዱ ቀዳማዊ የሰራተኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ተሊላ ደሬሳ ተናግረዋል።
የብድር ስምምነቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚዳንት ደርቤ አስፋው እና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።
በሀገሪቱ ካሉ ባንኮች ለብድር አገልግሎቱ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ምላሽ በመስጠቱ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አመስግነዋል።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው በበኩላቸው÷ ከአየር መንገዱ ጋር በርካታ ስራዎች እየሰሩ መሆኑን ገልጸው÷ በዛሬው እለት የብድር ስምምነት መፈራረማቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
በቅድስት ብርሃኑ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!