አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአፋር ክልል በመስኖ የበጋ ስንዴ የማምረት ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
በክልሉ እየተካሄደ ያለው በመስኖ የበጋ ስንዴ የማምረት ስራ ከውጪ የሚገባን ስንዴ የመተካት ጥረታችንን የሚያጠናክር አቅም አሳይቷልም ነው ያሉት።
በዚህም የዕድገት፣ የልማት እና የብልጽግና ሕልማችን እውን እንዲሆን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!