አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጀሪያ የሩሲያ አምባሳደር ከሆኑት ከኢጎር ቤልያኤቭ ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ም መንግስት በትግራይ ክልል ያከናወነው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁንና በክልሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ በመንግስትና በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ትብብር ለማድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታትድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር በስፍራው ተገኝተው ጉብኝት ማድረጋቸውንና በቀጣይ ሥራዎችም ዙሪያ ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተከሰተው የድንበር ግጭትም ታሪካዊ ዳራውን በመግለጽ ኢትዮጵያ ሱዳን ወደ ቀድሞዋ ሥፍራ ተመልሳ ድርድሩ መካሄድ እንዳለበትና ችግሩ ሊፈታ የሚችለውም በውይይት ብቻ መሆኑን እንደምታምን ገልጸዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያላትን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት አቋም ለሩሲያው አቻቸው መግለጻቸውን በአልጄሪያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!