አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመሀንዲስ ዋና መምሪያ ከ405 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሲገነባቸው የነበሩትን ሦስት ፕሮጀክቶች አጠናቆ ማስረከቡ ተገለጸ።
ርክክብ የተፈፀመባቸው ፕሮጀክቶች፣ 238.2 ሚሊዮን ብር የወጣበት የመከላከያ ማዕከላዊ ዴፖ፣ በ165 ሚሊዮን ብር የተገነባው የከባድ እና የቀላል ተሽከርካሪ የጥገና ማዕከል እንዲሁም ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የህፃናትና የእናቶች ማዋለጃ ህንፃ ናቸው ተብሏል።
ርክክቡን የፈፀሙት፣ የመሀንዲስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ጌታቸው ጉዲና፣ የህብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የጦር ኃይሎች ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ ብርጋደር ጀነራል ዶክተር ሀይሉ እንደሻው ናቸው።
በስነ ስርዓቱ ላይ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዔታ ጌታቸው ሀይለ ማሪያም፣ የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ታደሰ መኩሪያ እና ሌሎች አመራሮች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!