አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ፣ ሃዋሳ ከተማ እና ሆሳዕና ከተማ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድንና የለዉጡን ሂደት የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ እየሰጡ ባለው ጠንካራና በሳል አመራር በሀገሪቷ እየተመዘገበ ያለውን ለውጥ እንደሚደግፉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
በሃዋሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ከሲዳማ ክልላዊ መንግስት ወረዳዎች እና ከሀዋሳ ከተማ የተውጣጡ በርካታ ሰዎችተሳትፈዋል፡፡
የድጋፍ ሰልፉ በዲፕሎማሲ ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፍ ለተመዘገቡ ለውጦች እውቅና የሚሰጥ እና ባለፉት 3 ዓመታት ያመጡትን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚደግፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡
ሰልፈኞች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን መሆናቸውን የሚገልጹ መፈክሮችን ይዘው ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል፡፡
የሀዲያ ዞን ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት አመራር የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ሲሆን፤ ሰልፈኞቹ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጁንታውን ቡድን ለማምከን የሰጡትን በሳል አመራር እናደንቃለን፣ መንግሥት የጀመረው የለውጥ ጉዞ ከግብ እንዲደርስ የበኩላችንን እንወጣለን፣ የሀገር መከለከያ ሠራዊት ድል የኛም ድል ነው” የሚል መፈክር አሰምተዋል፡፡
በተጨማሪም ጁንታውን የማፍረሱ ድል የጋራ ጥረታችን ውጤት ነው፣ አደናጋሪ አሉባልታዎችን በማክሸፍ ለለውጡ ዘላቂነት እንተጋለን፣ ለውጡን የሚያደናቅፍ የሴራ ፖለቲካ እናወግዛለን” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል፡፡
ምንጭ፡- የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን እና የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!