የሀገር ውስጥ ዜና

አገራዊ የኮንስትራክሽን ሲምፖዚየምና ኤግዚቢሽን በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው

By Abrham Fekede

February 10, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የኮንስትራክሽን ሲምፖዚየምና ኤግዚቢሽን በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ በርካታ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች እንዲሁም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዙሪያ የተዘጋጁ ሰነዶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የንቅናቄ መድረኩ ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በመድረኩም ክልሎች፣ ከተማ አስተዳድሮችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂው የፈጠራ ውጤት ባለቤቶች እየተሳተፉ እንደሚገኝ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!