አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በኮሮና ምክንያት ትምህርታቸውን አቋርጠው የነበሩ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ፡፡
ዩኒቨርሲቲው የተማሪ ቅበላ ሲያደርግ ይህ ለሁለተኛ ዙር መሆኑም ተነግሯል።
የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በተለያዩ ጊዜያት በዩኒቨርሲቲው በመገኘት የተቋሙን የቅድመ ቅበላ ዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት ተመልክተዋል፡፡
ተማሪዎች ወደ ተቋሙ በገቡበት ወቅት በአካል በመገኘት ከመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመሆን አቀባበል አድርገውላቸዋል ።
ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ እስከ ተማሪዎቹ ቅበላ ድረስ ለተሰሩ ስራዎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፤ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በቅንጅት ሰርተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!