የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋር ክልል ህዝብና መንግስት ዘጠኝ ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ለትግራይ ክልል አስረከበ

By Abrham Fekede

February 10, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአፋር ክልል ህዝብና መንግስት ግምቱ ዘጠኝ ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ በትግራይ ክልል በመገኘት አስረከበ።

ድጋፉን የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤለማ አቡበከርን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በመቐለ ተገኝተው ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስረክበዋል።

የምግብ ቁሳቁሱ ሩዝ፣ ፉርኖ ዱቄት፣ ስኳርና ቴምር ሲሆን አጠቃላይ ብዛቱ 2 ሺህ 700 ኩንታል መሆኑ ተገልጿል።

የአፋር ክልል ላደረገው ድጋፍ በትግራይ ህዝብ ስም ምስጋና ያቀረቡት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ፤ “የአፋር ህዝብ የትግራይ ህዝብ ወንድም መሆኑን አሳይቷል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አቶ ኤለማ አቡበከር በበኩላቸው ክልላቸው ለትግራይ ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!