የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ ታደሰ የጨንቻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

February 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስተሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጋሞ ዞን የጨንቻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየሰጠ የሚገኘውን የጤና አገልግሎት ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት የሆስፒታሉን በተለይም የእናቶችና ህጻናት፣ የማዋለጃ እና የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ መመልከታቸውን አስታውቀዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብም የጤና አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል ላለው ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዲሁም በቁርጠኝነት ለሚያገለግሉት የሆስፒታሉ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ያሉትን ተግዳሮቶች በተቻለ አቅም በመፍታት የአገልግሎቱን ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል ይሰራልም ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!