አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በ36 ወረዳዎች በ92 የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የአስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ስርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
የኢትዮጵያ መንግስት ከ 26 በላይ ከሚሆኑ ዓለም አቀፍ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አፋጣኝ የምግብ ስርጭት ለማድረስ በትጋት እየሰራ ይገኛል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
70% የምግብ አቅርቦት በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን ቀሪው 30% ደግሞ በልማት አጋሮች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተሸፈነ ነው፡፡
እስካሁን ድረስ በክልሉ 2 ሚሊዮን 7 ሺህ ወገኖቻችንን ተጠቃሚ ተደርገዋል ነው ያለው፡፡
ለህፃናት፣ እናቶችና አረጋውያን የአልሚ ምግብ አቅርቦትን የበለጠ ለማስፋትና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶችን በተፈላጊው መጠን ለማቅረብ ከአጋር አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛልም ነው ያለው።
በቀጣይም የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ስርጭት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በሁሉም የክልሉ ማዕዘን ለሚገኙ የምግብ አቅርቦት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለመድረስ ያልተቆጠበ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብሏል የሰላም ሚኒስቴር፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!