አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኮቪድ19 ክትባትን በድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይም ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ ቻይና ለኢትዮጵያ ለምታደርው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለሀገራቸው አስፈላጊ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በክልላዊ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች የቻይና አጋር መሆኗን ነው የጠቀሱት፡፡
ኢትዮጵያ ኮቪድ19 ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ቻይና የበኩሏን ድጋፍ እንደምታደርግም ነው የገለፁት፡፡
ቻይና ቀጠናው እንዲረጋጋ ያላትን ፍላጎት ገልፀው በትግራይ ክልል የምግብ እህል ድጋፍ እንደምታደርግ እና ለአካባቢው ሰላም የድርሻዋን እንደምትወጣ አስታውቀዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!