አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኢፍ.ቢ.ሲ)የውጭ ሚዲያዎች ወኪል በመሆን ትሰራ ነበር የተባለችው ሉሲ ካሳ በሕጋዊነት ተመዝግባ እንደማትንቀሳቀስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በዘገባ ወቅት ባልታወቀ ግለሰብ ጥቃት ደረሰባት ብሎ የጠቀሳት ሉሲ ካሳ በኢትዮጵያ የውጭ ሚዲያዎችን በህጋዊነት የሚወክል ፍቃድ እንደሌላት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንን ጠቅሶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
መረጃ ማጣሪያው በአገሪቱ ሕገ መንግስት የትኛውም ግለሰብ በደህንነትና ነጻነት የመንቀሳቀስ መብቱ የተጠበቀ መሆኑንም ገልጿል።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞ ቡድን ፍሪ ላንስ ጋዤጠኛ ሉሲ ካሳ በዘገባ ወቅት ከምትዘግበው ሁነት ጋር በተያያዘ ጥቃት ደርሶባታል በሚል እንዲሁም በኢትዮጵያ የሎሳንጀለስ ታይምስ፣ አልጀዚራና የኖርዌይ ሚዲያ ወኪል ናት ብሎ መረጃ አውጥቶ ነበር ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የውጭ ሚዲያን በመወከል መንቀሳቅስ የሚፈልጉ ጋዜጠኞች በብሮድ ካስት ባለስልጣን በመመዝገብ ህጋዊ መሆንና የሚዲያ ይለፍ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል።
ይሁን እንጂ ሉሲ ካሳ በብሮድ ካስት ባለስልጣን ህጋዊ ምዝገባ አድርገው ከሚንቀሳቀሱ የውጭ ሚዲያ ወኪሎች መካከል አለመሆኗን ነው ያስታወቀው።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ሉሲ ካሳ አል ጀዚራን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሚዲያዎች በወኪልነት ትሰራ ነበር ብሎ ያወጣው መረጃም የተሳሳተ መሆኑን ገልጻል።
ቡድኑ መረጃ ከማሰራጨቱ በፊት የመረጃውን እውነተኝነት ግራና ቀኝ አጣርቶ ማውጣት እንደነበረበት ነው ያመለከተው።
በአገሪቱ ሕገ መንግስት ማንም ሰው በነጻነትና ደኅንነቱ ተጠበቆ የመንቀሳቀስ እንደሚችል መደንገጉን ገልጾ ቡድኑ በተሳሰተ ሁኔታ ያሰራጨውን መረጃ በአስቸኳይ እንዲያርም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው አሳስቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!