የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ ጂቡቲ የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

February 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ ጂቡቲ የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ኢትዮጵያና ጂቡቲ ጥብቅ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዘርፉ የሃገራቱን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ፎረሙ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለውም ተገልጿል፡፡

የጅቡቲ የቱሪዝም ሚኒስትር መሐመድ አብዱልቃድር ሙሳ በበኩላቸው የሃገራቱን ህዝቦች ትስስር ለማጠናከር በመንግስታቱ ብዙ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በፎረሙ የሃገራቱን እምቅ የቱሪዝም ሃብት የሚያመላክቱ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!