አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ በኢትዮጵያ ከኖርዌይ አምባሳደር መረተ ሉንደሞ ጋር ተወያዩ፡፡
ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያና በኖርዌይ የጋራ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይታቸው በኃይል፣ በዘላቂ የልማት ግቦች፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በደን ልማት እና በጾታ እኩልነት ላይ ትኩረት ማድረጉን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የቀጠለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይም ማብራሪያ መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም ግድቡ ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው የገለጹት ሚኒስትሩ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን የኃይል አቅርቦት እንደሚያሳድግ በዚሁ ወቅት ለአምባሳደሯ አስረድተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!