የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በጅግጅጋ የከተማ ልማት ስራዎችን ጎበኙ

By Abrham Fekede

February 11, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የከተማ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የመንገድ ስራዎችንም መመልከታቸው ነው የተገለጸው፡፡

እንዲሁም ከፕላን ጋር በተያያዘ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በነገው ዕለትም በጅግጅጋ ከተማ የክልላዊ ስፓሻል ልማት ፕላን ዝግጅት ማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ የሚነጋገር መድረክ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!