የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የዑለማዎች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ

By Abrham Fekede

February 11, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የዑለማዎች ምክር ቤት አባላት ጋር ውይይት አካሄዱ፡፡

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከምክር ቤቱ በቀረበ ጥያቄ መሰረት ውይይቱን ማካሄዳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም ከፌደራል የእስልምና ጉዳዮች ቦርድ አባላት እና ከአንዳንድ የክልልና የከተማ አስተዳደር የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቶች ዑለሞችና ቦርድ አባላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

በውይይቱ በተጀመሩ የተቋማዊ ለውጥ ተግባራትና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች በመፋትሄ አቅጣጫዎች ላይ  በስፋት ምክክር ማድረጋቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!