የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ከተመድ የስራ ኃላፊዎች ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

February 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል የኦፕሬሽን ዳይሬክተር እና ከተመድ የዘር ማጥፋት መከላከል ልዩ አማካሪ ጋር በተናጠል የቪዲዮ ውይይት አካሂደዋል።

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከአለም አቀፉ የቀይ መስቀል የኦፕሬሽን ዳይሬክተር ዶሚኒክ ስቲልኻርት ጋር ተወያይተዋል።

አለም አቀፋ የቀይ መስቀል ማህበር በኢትዮጵያ ስለሚያደርገው ተከታታይ ድጋፍ አምባሳደሩ አመስግነዋል።

በትግራይ ክልል የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ እና መልሶ ማቋቋም ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በውይይታቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል አምባሳደሩ ከተመድ የዘር ማጥፋት መከላከል ልዩ አማካሪ አሊስ ዋይሪሙ ጋር መክረዋል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሁሉም ህዝቦች መብት የሚከበርበትን ስራ እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!