የሀገር ውስጥ ዜና

ፖሊስ በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ 113 የምስክርና በርካታ ማስረጃ መሰብሰቡን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

February 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖሊስ በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ 113 የምስክርና በርካታ ማስረጃ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

እነ ስብሃት ነጋ ዛሬ ለሶስተኛ ጊዜ በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ፍርድ ቤቱ የእነ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር አባይ ወልዱና ዶክተር አብርሀም ተከስተን ጨምሮ የሌሎችንም ተጠርጣሪዎች ጉዳይ ተመልክቷል፡፡

በተጨማሪም ችሎቱ በማይካድራ በንጹሀን ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 36 ተጠርጣሪዎችን ጉዳይም እየተመለከተ ነው፡፡

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!