አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከአዲሱ ገበያ – በቀጨኔ – ሽሮሜዳ አድርጎ መዳረሻውን መገናኛ የሚያደርገው የቀለበት መንገድ ግንባታ በታቀደለተ ጊዜ ባለመጠናቀቁ በአካባቢው ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ተናገሩ።
በአሁኑ ጊዜ መንገዱ ከታቀደለት ውጭ የመኪና ማደሪያ መሆኑን አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
መንገዱ በታቀደለት መልኩ ቢገነባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ እንደሚቀርፍም ነው አስተያየት ሰጭዎቹ የሚናገሩት፡፡
በተለይም በክረምት ወራት የፍሳሽ መውረጃዎቹ በተለያዩ ቆሻሻዎች ስለሚደፈኑ መንገዱ ለጉዳት ከመዳረጉም ባለፈ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑንም ይገልጻሉ።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ እያሱ ሰለሞን
በሰጡት ምላሽ፥ የመንገዱን 4ኛ ምዕራፍ ለማጠናቀቅ 8 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የአካባቢው መልክዓ ምድር አቀማመጥ የቀለበት መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ችግር እንደፈጠረም አውስተዋል፡፡
በተጨማሪም ቀለበት መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው 8 ቢሊየን ብር በባለስልጣኑ አቅም የሚሟላ ባለመሆኑ ከሌላ አካል እገዛ እየተፈለገ ነው ብለዋል።
የቀለበቱ መንገዱ ተለዋጭ የዲዛይን ለውጥ እንደሚያስፈልገው በመጥቀስም እስካሁን 38 ኪሎ ሜትር መሰራቱን አስረድተዋል፡፡
በሚቀጥለው በጀት ዓመትም የቀለበት መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በሲሳይ ጌትነት
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!