አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ የተካሄደውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ተከትሎ ህብረ-ብሔራዊነትን በጠበቀ መልኩ አዲስ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ መደረጉን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል።
በህዝብ በማስተቸት የከፋ ችግር የታባታቸውን አመራሮች በማንሳት በአዲስ እንዲተኩ በማድረግና የከፋ ችግር የሌለባቸውን ደግሞ በማሸጋሸግ የመተከል ዞንና ወረዳዎች መዋቅር መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ብሏል ፓርቲው በመግለጫው።
በዚሁ መሰረት የመተከል ዞን መምሪያ መዋቅር መልሶ ለማደራጀት በተወሰደ የመፍትሔ እርምጃ የትምህርት መምሪያ፣ የከተማ ልማት እና የንግድ መምሪያ፣ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ፣ ፍትህ መምሪያ እንዲሁም የውሃና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ቦታ ላይ የአመራር አድስ ምደባ እና ሽግሽግ ስራ ተሰርቷል ነው ያለው።
የወምበራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ መደረጉ ተገልጿል።
የቡለን ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።
የድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።
የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል ሲል ፓርቲው ገልጿል።
የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።
በተመሳሳይ የካቢኔ እና የጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች ላይ የአመራር አዲስ ምደባ እና የማሸጋሸግ ስራ በመስራት መልሶ የማዋቀር ስራ ተሰርቷል ብሏል።
እንደፓርቲው ገለጻ፦
መተከል ዞን፦ 1. አቶ መልካሙ ባሽዋል ከመተከል ዞን ከተማ ልማትና ንግድ መምሪያ ኃላፊ ወደ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 2. አቶ ተክሌ ዋኔያ የመተከል ዞን ውሃና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ሆና በአዲስ ተሹሟል። 3. አቶ ገበየሁ ጀጎዴ ከመተከል ዞን ውሃና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ወደ ከተማ ልማትና ንግድ መምሪያ ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 4. አቶ አበበ እንድሪስ የፓዊ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ የነበረ የመተከል ዞን ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ ሆኖ ተሹሟል። 5. ወ/ሪት ቃልኪዳን ቶማስ የመተከል ዞን ፍትህ ኃላፊ ሆነው ተሹሟል። በመተከል ዞን ወረዳ የአመራሮች አዲስ ምደባና ሽግሽግ በዋናነት፦ ወምበራ ወረዳ፦ 1. አቶ ሙሉጌታ አዲሱ ከወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ወደ ዋና አስተዳዳሪ ተሸጋሽጓል። 2. አቶ ገመዳ ዱጋስ ከግልገል በለስ ከተማ መሬት አስተዳደር ላይ የነበረ የወምበራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ሆኖ ተሹሟል። 3. አቶ አምሳሉ ቢፍቱ የወምበራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሾሟል። 4. አቶ በዛብህ ጉደታ የወምበራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበረ ወደ አካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደር ኃላፊ ሆኖ ተሸጋሽጓል። 5. አቶ ባይሳ ጉርሳ ከደብረዘይት ከተማ ስራ አስኪያጅ ወደ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 6. አቶ ተሻለ አረጋ ከወምበራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወደ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 7. ወ/ሮ ኩሉሌ ነገዎ የወምበራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 8. አቶ አርጋታ አድማሱ የደብረዘይት ከተማ ስራ አስኪያጅ ሆነ በአዲስ ተሹሟል። 9. አቶ ድሪባ ገመቹ የሶንኮራ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅ ሆኖ በአዲስ ተሹመዋል። 10. ወ/ሮ አበባ አዳመ የወምበራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። አቶ ምትኩ አለማየሁ የወምበራ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ መ/አስ/ኢን/ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩትን ጨምሮ አራት አመራሮች ከሀላፊነት ተነስተዋል። ቡለን ወረዳ፦ 1. አቶ አሳየ ዳዮ የቡለን ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳደሪ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 2. አቶ ካሳሁን አዲሱ ከቡለን ወረዳ መንግስት ኮ/ባ/ቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ወደ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 3. አቶ ወንዲፍራው አለነ ከግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 4. አቶ አብዲሳ ተሰራ የአካባቢ ጥበቃ መ/አስ/ኢን/ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ ተሹሟል። 5. አቶ አምሳሉ የቆየ የቡለን ወረዳ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 6. አቶ ታደሰ ነጋሽ ንግድ ኢ/ት/ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 7. አቶ ታደሰ ጋሹ ከትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወደ ቡለን ወረዳ መንግስት ኮ/ባ/ቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 8. አቶ አዳሙ ቀናኦ የቡለን ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 9. አቶ ዱሹ ቦካ ከሚኒሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ወደ ቡለን ወረዳ ፀጥታና ሰላም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 10. አቶ ዶክተር ጃላታ ከትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወደ ቡለን ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 11. አቶ ስሜነህ ባግዴ ከቡለን ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዘርፍ ኃላፊ ወደ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 12. አቶ ሂካ መኮንን ጤና ጽ/ቤት ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 13. ወ/ሮ ትግስት አድማሱ የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። በቡለን ወረዳ ከላይ የተዘረዘሩትን ጨምሮ 19 የአመራር ሽግሽግና አዲስ ሹመት ተሰጥቷል። ድባጢ ወረዳ፦ 1. አቶ ሀይማኖት ጎበና የፀጥታና ሰላም ግንባታ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 2. አቶ ዳምጤ ጎበና ከትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወደ ድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ተሸጋሽጓል። 3. አቶ ሀብታሙ አርጋታ ከድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ወደ ም/ዋና አስተዳዳሪ ተሸጋሽጓል። 4. አቶ ሀይሉ በቀለ ከጤና ምክትል ኃላፊ ወደ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ተሸጋሽጓል። 5. አቶ አስረሳ እያሱ ሰ/ማ/ዋ ስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 6. አቶ ዋርብ ሙሀመድ የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 7. አቶ አንተነህ ንጉሴ የድባጢ ወረዳ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 8. አቶ ዋሽንግት ወምፑ የድባጢ ወረዳ የውሀ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 9. አቶ ታፈረ ሰንበታ ከግብርና ተፈጥሮ ሀብት ምክትል ኃላፊ ወደ ድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ተሸጋሽጓል። 10. አቶ ኡመር ካንቲ የድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ፋይናንስ ዘርፍ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። ከላይ የተዘረዘሩትን ጨምሮ በወረዳው 17 አዲስ አመራር ምደባና ሽግሽግ ተደርጓል። አቶ ተወካይ ብርሀን የድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊን ጨምሮ 15 አመራሮች ከኃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ማንዱራ ወረዳ፦ 1. አቶ ቢምር አምሳያ የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆኖ ተሹሟል። 2. ወ/ሮ የኔነ ሽውዋ ከጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወደ የወረዳው ዋና አፈ-ጉባዔ ህኖ ተሸጋሽጓል። 3. አቶ አስፋው ወርቅነህ የማንዱራ ወረዳ መንግስት ኮ/ባ/ቱ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። 4. አቶ በሊና ጌታሁን ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በአዲስ ተሹሟል። ከላይ የተዘረዘሩትን ጨምሮ በወረዳው 15 አዲስ አመራር ምደባና ሽግሽግ ተደርጓል። ወ/ሮ አልጊና ዊሊያም የማንዱራ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤን ጨምሮ 9 አመራሮች ከኃላፊነት እንዲነሱ ተወስኗል። ጉባ ወረዳ፦ 1. ወ/ሮ ቡሴና ረጀብ የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ሆኖ ተሹሟል። 2. አቶ ባኬ ዱርዱም የጉባ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!